eotcgbg.org

Gothenburg St. Gebriel ETOC

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንበዮተቦሪ ደ/ኃ ቅ/ገብርኤል እና ቅ/ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን

ታሪክ

እኛ በልዩ ልዩ ምክንያት ከሀገራችን ከኢትዮጵያ የወጣን በስዊድን ጉተንበርግና አካባቢዋ የምንኖር የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ !!!

ተዋሕዶ ሃይማኖት ዕምነት ተከታዮች በልዑል እግዚአብሔር ፈቃድ ተሰባስበን በሄድንበት ሁሉ የሚመራንንና
የሚጠብቀንን በቦታ የማይወሰን አምላካችንን ስሙን ጠርተን እንድናመሰግን በአለንበት አገር ቤተክርስቲያን ማዘጋጀት
ኃይማኖታዊ ግዴታችን እንደሆነ በመገንዘብ ገንዘባችንን፤ ዕውቀታችንንና ጉልበታችንን አስተባብረን የእግዚአብሔርን
ቃል የምንማርበት፤ ስሙን ጠርተን የምንጸልይበት በደብረ ኃይል ቅ/ገብርኤል ስም ሕንጻ ቤተክርስቲያን ገዝተን
አገልግሎት ላይ ካዋልን ዓመታት እየተቆጠሩ ነው። ይህ መካነ ጸሎት የዘርና የቋንቋ ልዩነት ሳይኖር የኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ሃይማኖት ዕምነትን የሚከተል ሁሉ በእኩልነት የሚጠቀምበት ነው። የእግዚአብሔር ቤት አንድ እምነት ላለው
ሁሉ ቤቱ ነውና።

የደብረ ኃይል ቅ/ገብርኤል ቤተክርስቲያን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1992 ዓ.ም ጀምሮ ከተለያዩ
አብያተክርስቲያናት በኪራይ የምናደርገውን መሰባሰባችንን ባርኮልን ከሐምሌ 2010 ዓ ም ጀምሮ አሁን
የምንጠቀምበትን ቤተክርስቲያን ከሶርያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ወንድሞቻችን በመግዛት በሐምሌ 19 ቀን 2010
በከፍተኛ ድምቀት ታቦተህጉ ተባርኮና ደብረ ኃይል ቅ/ገብርኤል ቤተክርስቲያን በሚል ስያሜ የቀጠለ ሲሆን በስዊድን
በመንግስትም በ “May 21, 2015 Debre Haile St. Gabriel Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
organizational no. 252004-8451”

በመባል ተመዝግቧል ሆኖም ግን የምዕመናኑ መጠናከርና ከቤተክርስቲያናችን እድገት ጋር ተጨማሪ ታቦት
በማስፈለጉ

በምዕመናኑ ጥያቄ በዕጣ የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦት በመውጣቱ በደባልነት ገብቶልንና በሚያዝያ 23 ቀን
2013 ዓ.ም. ተባርኮልን የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤልና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተብሎ ይኸው አገልግሎቱን
በጉተንበርግና አካባቢው ለሚገኙ ምዕመናን በተዋሕዶ እምነትና ሥርዓት መሠረት አገልግሎቱ በሰፊው መስጠቱን
ቀጥሏል።

Leave a Reply

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው